Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 12, 2025 at 04:36 PM
*የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ ተጠናቀቀ፤*
(የካቲት 05/2017 ዓ.ም) በትንትናው ዕለት የጀመረው የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።
የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት የሚያስችል ጉዳዮች ላይ በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።
በውይይቱም የሁለትዮሽ ረቂቅ የመመስረቻ ሰነድ ላይ የተለያዩ ግብዓቶችን በመጨመር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለፊርማ ዝግጁ እንዲሆን ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በሁለት ቀናት የውይይት ቆይታ ላይ በጋራ ለመስራት በተስሟሟቸው አጀንዳዎች ዙሪያ በመፈራረም እና የጋራ መግለጫ በመስጠት ተጠናቋል።