Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 13, 2025 at 12:52 PM
የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መመስረቻ ዉይይት ተሳታፊዎች የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከልን ጎበኙ የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መመስረቻ ዉይይት ተሳታፊዎች የማስፋፊያዉ ግንባታ እየተጠናቀቀ ያለዉን የሞጆ ወደብ የሎጂስቲክስ ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ የጅቡቲ መሰረተ-ልማት እና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ሀሰን ሀሙድ፣ የጅቡቲ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር መሀመድ ዋርሳማ፣የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሐሰን፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ አብዱልበር ሸምሹ እና ሌሎች የሁለቱ ሀገራት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በጉብኙቱ ወቅት አጠቃላይ የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል አገልግሎት ፣ የቀዝቃዛ ሎጂስቲክስ አና ተጨማሪ መጋዘን የማስፋፊያ ግንባታን በተመለከተ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል ቺፍ ኦፕሬሽን አቶ ደረጀ ሚደቅሳ ገለጻ አድርገዋል። ጎብኚዎቹም በተመለከቱት የማስፋፊያ ግንባታ እና የወደቡ አገልግሎት መደነቃቸዉን ተናግረዋል።
😢 1

Comments