Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 14, 2025 at 02:47 PM
የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ አዲስ አበባ ገቡ፤ (የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ ) የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ 38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
👍 🙏 2

Comments