
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 14, 2025 at 05:04 PM
በጅቡቲ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ የልማት ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፤
—————————————
(የካቲት 07/2017 ዓ.ም) የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር ከበደ አበራ ነዋሪነታቸው በጅቡቲ ካደረጉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ወቅታዊ በሆኑ የልማት እና ሰላም ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በመድረኩም በሀገራችን ስላለው የሰላም እና የልማት እንቅስቃሴዎች፣ በሁሉም ክልል ስለተጀመሩ የኮሪደር ፕሮጀክቶች፣ እየተስፋፋ ስላለው የቱሪዝም መስክ እና በጅቡቲ የዜጎቻችንን ህገ-ወጥ ዝውውር መከላከል ላይ ከእያንዳንዱ የዳያስፖራ አባል የሚጠበቀው ኃላፊነትን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ተሳታፊዎች በሀገራችን የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች የሚበረታቱ መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ ባጋጠሟት በርካታ ፈተናዎች ሳትበገር፣ ለትውልድ የሚሆን አሻራን እያስቀመጠች በመሆኑ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በፖሊሲ የተደገፈ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።
በውይይቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከተለያዩ የልማት ማህበር አደረጃጀቶች የተውጣጡ የዳያስፖራ አባላት፣ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል።
👍
😮
3