Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 18, 2025 at 06:20 AM
የምግብ ዘይት ኦፕሬሽን ስራ በኮንቴነር መላክ ተጀመረ፤ ላለፉት ጊዜያት ከጂቡቲ ነጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ሲላክ የነበረው የምግብ የዘይት ኦፕሬሽን ስራን ለማቀላጠፍ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ባቡሩ ላይ በቋሚነት በመቀመጥ የብትን ኮንቴይነር ካርጎ Bulk Cargo Container (BCC) አሰራር ስርዓት በመዘርጋት ዘይት መጫን ተጀምሯል። ከዚህ ቀደም በመደበኛ የምግብ ዘይት ኦፕሬሽን ስራ እና ሌሎች የገቢ-ወጪ ጭነቶችን ለማስተናገድ ባቡሩ ላይ ባለው ቋሚ ዋገን ብቻ ሲጫን የነበረ ሲሆን፣ የባቡር ፕሮጀክቱን ለማስፋት ዕቃ ጭነው የመጡ ከ500 በላይ ኮንቴይነሮች (BCC) ጅቡቲ አገልግሎት ላይ ሳይውሉ ለረጅም ዓመታት መቆየታቸውን በመገንዘብ ኤምባሲው ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ድርጅት ጋር በመተባባር በዘርፉ የሚመለከታውን የሁለቱ አገራት ተቋማትን በማወያየትና ከስምምነት በመድረስ የፉርጎ-ኮድ ተሰጥቷቸው በባቡሩ ተጎታች ላይ ሆነው (Wagons) አገልግሎት በሁለቱ አገራት ብቻ እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በመሆኑም አሁን የተጀመረው የቋሚ ኮንቴነር ጭነት ስርዓት፣ ከዚህ ቀደም በዋገን እጥረት ምክንያት የሚፈጠረውን መዘግየት እና የጭነት መጠን በማሻሻልና በማሳደግ ጭምር የዘይት ኦፕሬሽን ስራው በብዛት እና በተቀላጠፈ መልኩ እንዲካሄድ ለማድረግ ያግዛል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ድርጅት የጀመረው አሰራር የብትን ጭነቶች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲጓጓዙ ከማገዙም በላይ የባቡሩንም ውጤታማነት የሚያሳድግ ሆኗል፡፡
👍 1

Comments