
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 26, 2025 at 05:55 PM
ክቡር አምባሳደር ከጂቡቲ ኢንቨስትመንት እና የግል ሴክተር ልማት ሴክሬተሪ ኢን ቻርጅ ጋር ተወያዩ፤
ክቡር አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ ከጂቡቲ ኢንቨስትመንት እና የግል ሴክተር ልማት ሴክሬተሪ ኢን ቻርጅ ክብርት ሳፊያ መሀመድ አሊ ጋር በሁለቱ አገራት የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት እና የኢንቨስተሮች ልውውጥ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ግንኙነት በማንሳት ይህን ግንኙነት ለማጠናከር የተለያዩ የጉብኝቶችን እና የተቋማት ጉድኝት ስራዎችን ለመስራት ተነጋግረዋል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚካሄደው የ2025 ኢንቨስት ኢትዮጵያ ፎረም ላይ ለመሳተፍም ተስማምተዋል።
❤️
1