Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 28, 2025 at 08:50 AM
የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ (DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፤ (የካቲት 20/2017 ዓ.ም) በትንትናው ዕለት የጀመረው የኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ምስረታ ሚንስትሮች መድረክ የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ (DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። በትናንትናው ዕለት የጀመረው ይህ መድረክ በቴክኒካል ኮሚቴው በረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል። እንዲሁም የኮሪደሩ አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት የሚያስችል ጉዳዮች ላይም ቴክኒካል ኮሚቴው ሰፊ ውይይት አድርጓል። የኮሪደሩ መመስረት የኮሪደር በተሳታፊ አገሮች መካከል የመሰረተ-ልማት ትስስር በመፍጠር፣ ትብብርን በማስፋፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማጎልበት ክልላዊ ውህደትን ለማጠናከር የሚረዳ ይሆናል።
❤️ 👍 2

Comments