
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 28, 2025 at 08:54 AM
129ኛው ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በጂቡቲ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ፤
__________________________________
(የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.) በጂቡቲ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢምባሲ አዘጋጅነት “አድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል 129ኛው ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በኤምባሲው የመከላከያ ሰራዊት አታሼዎች፣ በጂቡቲ ያሉ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት፣ ከሀይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ተከብሯል።
የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ በመክፈቻ በንግግራቸው አድዋ በዓል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም የጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑን በመግለጽ ይህን ታሪክ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አንስተዋል።
የፓናል ውይይቱ በኤምባሲው መከላከያ አታሼ ስለ አድዋ በዓል የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታየው አንድነት በሌሎች ሃገራዊ ስራዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል ።
በመድረኩም የአድዋን ገድል የሚያትት አጭር ተውኔት፣ የኬክ ቆረሳ እና በባህላዊ ውዝዋዜ በድምቀት ተከብሯል።
❤️
👍
2