Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
May 12, 2025 at 04:33 PM
የአርቲስቶች ልዑክ በትምህርት ቤት ላይ ከኤምባሲው ጋር እንደሚሰራ ገለጸ፤ (ግንቦት 04/2017 ዓ.ም) በጂቡቲ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ለሀገራችን አርቲስቶች ልዑክ አቀባበል ያደረገ ሲሆን፣ የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር ከበደ አበራ በተለያዩ ማህበራዊ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ከልዑኩ ጋር ውይይት አድርገዋል። ምክትል የሚሲዮን መሪው ለልዑኩ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው አርቲስት ማለት ለማህበረሰቡ እና ለሀገሩ ድምጽ የሚሆን በመሆኑ፣ ሚሲዮኑ በጂቡቲ በሚያደርጋቸው ማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይ በማሰተፍ ድምጽ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። በተለይም ደግሞ በጂቡቲ የተጀመረው የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ ላይ በሙያቸው በመሳተፍ ለትውልድ የሚሆን አሻራ እንዲያኖሩ አሳስቧል። ልዑኩ በበኩሉ በኤምባሲው ስለተደረገለት አቀባበል በማመስገን፣ በጂቡቲ የትምህርት ቤት ግንባታ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ባህል፣ ቋንቋ እና እሴት የሚያጠናክር እና ከምንም በላይ የነገ ትውልድ የሚቀረጽበት ተቋም በመሆኑ ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። በቀጣይም በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል። Telegram: https://t.me/EthiopiaInDjibouti/2704

Comments