
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
May 14, 2025 at 04:13 AM
የሳምንቱ #humanrights Concept: ቤተሰብ የመመሥረት መብት
...
ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 16 (1) እና (2)
ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሰ ወንዶች እና ሴቶች በዘር፣ በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው ጋብቻ የመፈጸም እና ቤተሰብ የመመሥረት መብት አላቸው። ጋብቻው ሲፈጸም፣ በጋብቻ ወቅት እና ጋብቻው በሚፈርስበት ጊዜ እኩል መብቶች አሏቸው።
ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻ እና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሠረታል።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 34 (3)
ቤተሰብ የኅብረተሰብ ተፈጥሯዊ እና መሠረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው።
🔗 https://ehrc.org/?p=32750
#ethiopia🇪🇹 #keepwordsafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።