Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
May 18, 2025 at 09:29 AM
የሴት ልጅ ግርዛትን አስመልክቶ በሚካሄድ ግልጽ የምርመራ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት ... በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛት እና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ማኀበረሰብን ማንቃት፣ ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረግ እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሴት ልጅ ግርዛት ላይ ስለሚያካሂደው ግልጽ የምርመራ መድረክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዓላማ የግልጽ ምርመራ መድረኩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ማሳወቅ እና አስፈላጊ በሆኑ በትብብርና እገዛዎች ላይ መወያየት ነው። በውይይቱ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከአፋር እና ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ፍትሕ ቢሮ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጤና ቢሮ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የሀዲያ ዞን ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ፣ የፍትሕ፣ የፖሊስ እና ጤና ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች የሴቶች እና የሕፃናት መብቶች ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። 🔗 https://ehrc.org/?p=32857 #ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Image from Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ: የሴት ልጅ ግርዛትን አስመልክቶ በሚካሄድ ግልጽ የምርመራ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት ......

Comments