
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
May 21, 2025 at 03:34 PM
በሕክምና ተቋማት ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሥራ ማቆም አድማ በተመለከተ
...
በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት ሊሰጣቸው እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል።
ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኢሰመኮ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ከአጋሮ፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከባሕር ዳር፣ ከፍቼ፣ ከጎባ፣ ከሃዋሳ እና ከጅማ ከተሞች መረጃ ማሰባሰብ ችሏል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33103
#ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
