Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
May 26, 2025 at 02:30 PM
የትምህርት መብት፡- በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት ... የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የትምህርት ግብአት አቅርቦት፣ ከባቢያዊ እና የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም የአመለካከት ክፍተቶች ላይ መሥራት ያስፈልጋል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ባሕር ዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ባኮ፣ ጋምቤላ፣ ሆሳዕና፣ መቐለ፣ ሰበታ እና ሻሸመኔ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሁለት የምክክር መድረኮች በአዲስ አበባ እና ሃዋሳ ከተሞች አካሂዷል። በውይይት መድረኮቹ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ የጋምቤላ፣ የኦሮሚያ እና የሲዳማ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች፣ ጽሕፈት ቤቶች እና ክትትል የተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል። ኢሰመኮ በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የአዲስ አበባ እና የባሕር ዳር ከተሞች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ተመሳሳይ የውይይት መድረክ በመጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄዱ ይታወሳል። ‎🔗 https://ehrc.org/?p=33164 ‎ ‎#ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall ‎ ‎በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Image from Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ: የትምህርት መብት፡- በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት ...  የአካል ጉዳ...

Comments