
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
May 30, 2025 at 11:51 AM
5ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (Human Rights Moot Court) ፍጻሜ ውድድር ተካሄደ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 5ኛውን ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (5th National High Schools Human Rights Moot Court Competition) ፍጻሜ ውድድር ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። ከሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ በቆየው ውድድር በ12 ክልሎች እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች ከሚገኙ 90 ትምህርት ቤቶች 180 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
በዚሁ መሠረት ተማሪ ሲፈን ደረጄ እና ተማሪ ሚልኬሳ ንጋቱ ከቢሾፍቱ ከተማ የኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ የፍጻሜ ውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል። በተጨማሪም የውድድሩ ምርጥ የቃል ተከራካሪ በመሆን ተማሪ ሲፈን ደረጄ ከኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ ያሸነፈች ሲሆን በምርጥ የጽሑፍ ክርክር ደግሞ በተመሳሳይ ከኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ የመጡት ተማሪ ሲፈን ደረጄ እና ተማሪ ሚልኬሳ ንጋቱ አሸናፊዎች ሆነዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33257
#ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
