Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
June 2, 2025 at 02:49 PM
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት መብቶች አያያዝ ላይ የተካሄደ ውይይት ... በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻዎች ምክረ ሐሳቦችን በቅንጅት ሊተገብሩ ይገባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሃዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ወላይታ ከተሞች በሚገኙ 21 የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ባከናወነው የምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ክትትል ግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሴቶች፣ የሕፃናት እና የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ኃላፊዎች እንዲሁም የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል። ኢሰመኮ በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ከሚገኙ ሕፃናት መብቶች አያያዝ ጋር በተያያዘ ያከናወነው ክትትል ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ማዕቀፎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን፤ በተለይም የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የቅበላ መሥፈርቶች እና መረጃ አያያዝ፣ የሕፃናት ከጥቃት የመጠበቅ መብት፣ የቅጣት (የዲሲፕሊን) እርምጃዎች​፣ የጤና፣ የሥነ ልቦና፣ የትምህርት፣ የጨዋታ እና የመዝናኛ አገልግሎቶች፣ የእምነት ነጻነት እና የተሳትፎ መብቶችን በተመለከተ የተለዩ ግኝቶች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። 🔗 https://ehrc.org/?p=33299 #ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Image from Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ: በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት መብቶች አያያዝ ላይ የተካሄደ ውይይት ...  በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ...

Comments