Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
June 4, 2025 at 03:00 AM
የሳምንቱ #humanrights Concept: በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የተጎዱ ሕፃናት ... የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 39 ተዋዋይ ሀገራት የማናቸውም ዐይነት የእንክብካቤ እጦት፣ ብዝበዛ፣ ያልተገባ አያያዝ፣ ማሰቃየት ወይም ሌላ ማናቸውም ዐይነት ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ወይም የትጥቅ ግጭት ሰለባ የሆነን ሕፃን በአካልና በሥነ ልቦና ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግምና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ዐይነቱ ሕፃኑን ከጉዳቱ እንዲያገግም እና ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀል የማድረግ ተግባር የሕፃኑን ጤንነት፣ ለራስ ዋጋ የመስጠት ስሜት እና ክብር ለማዳበር በሚያመች ሁኔታ ውስጥ መከናወን አለበት። 🔗 https://ehrc.org/?p=33355 #ethiopia🇪🇹 #keepwordsafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Comments