Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
May 27, 2025 at 04:14 AM
የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራ ከቁጥር ባለፈ ትርጉም ባለው መንገድ የዜጎችን ህይወት ሊቀይር እንደሚገባ ተገለፀ። የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ75 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉትና የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም ከስኬት ባንክ ጋር በመቀናጀት በባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች የተደረገ ኦዲት ሪፓርት በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በግምገማ መድረኩ በዘጠና ቀናት የንቅናቄ ዕቅዱ በ35ኛው ቀን የግምገማ መድረክ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀምን ጨምሮ በ75 ቀናቱ በስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉት ስራዎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ቀርቧል። ባለፉት 75 ቀናት በስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉት ንቅናቄ ስራ በተከናወኑ ተግባራት በበጀት ዓመቱ ለመፍጠር ከታቀደው 300ሺ የስራ ዕድል ፈጠራ በ10 ወራት ከ15 ቀናት ውስጥ ብቻ 324ሺ282 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉ ተገልጿል። ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞችን በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርአት E-LMIS ከመመዝገብ አንፃር 13ሺ15 ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት መቻሉንና አሁንም ከውጤታማነት አንፃር ክፍተት መኖሩ ተገልጿል። በሌማት ትሩፋት 2ኛ ዙር ንቅናቄ መርሀ ግብር አምስት ግቦች ተጥለው ወደ ተግባር መገባቱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለ9ሺ528 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩ ተመላክቷል። በንቅናቄ በተሰራው ስራ የግብአት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ጥረት መደረጉንና የከተማ ግብርና ስራ ባህል እየሆነ መጥቷል ተብሏል ነገር ግን ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ ዋጋ ከማረጋጋት አንፃር አሁንም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። የግምገማ መድረኩ ሌላኛው የትኩረት ነጥብ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ ስኬት ባንክ እያደረገ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት እንዲሁም ብድር ለመስጠት የባንኩ ቅድመ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ የሚለውን በመዳሰስ ከብድር ፈላጊዎች ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ አለመቅረብ አንዱ ተግዳሮት መሆኑ ተገልጿል። የውይይት መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራ ከቁጥር ባለፈ ትርጉም ባለው መንገድ የዜጎችን ህይወት ሊቀይር ይገባል ብለዋል። አቶ ጥራቱ አያይዘውም በየጊዜው በተካሄዱ የግምገማ መድረኮች በክፍለ ከተሞች መካከል የፉክክር መንፈስ በመፍጠር በአፈፃፀም ዝቅተኛ የነበሩ ጽሕፈት ቤቶች ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት ስራውን ከሌሎች ተግባራት ጋር አቀናጅቶ በምራት የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ያለውን አስተዋፅኦ በመረዳት በትኩረት መሰራት እንዳለበትም በመድረኩ ተጠቁሟል። የግምገማ መድረኮቹ ዓላማ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜያት ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ መቀመጡን ከቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 19፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

Comments