Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
May 30, 2025 at 09:43 AM
የደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት አገኘ ኮሌጁ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬቱን ተረክቧል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን እንዳገኘ አመላክቷል። በርክክብ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት አስተላልፈው መንግስት ለጥራት ልዩ ትክረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መገልገያ መሳርያዎችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ  መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 22፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com
Image from Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia: የደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት አገኘ   ኮሌጁ ከኢትዮ...

Comments