
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 14, 2025 at 12:07 PM
ኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር በልዩ የኢኮኖሚ ዞን የአንድ መስኮት አገልግሎት ስራ አስጀመረ፤
በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ይፋ የተደረገውን የአንድ መስኮት አገልግሎት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታከለ ኡማ (ኢ/ር) እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አገልግሎቱ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ዉስጥ ለሚገኙ ከፍተኛ ምርት ላኪዎች አማራጮችን እያሰፋ ፣ የሎጅስቲክ ተግዳሮትን እየፈታ የገቢ እና ወጪ ንግዱን በማሳለጥ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
አክለውም የአንድ መስኮት አገልግሎቱ በቀጣይም በሌሎች ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እንደሚቀጥል ጠቁመዋል::
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ መጀመር በልዩ ዞኑ የሚገኙ ባለሀብቶችን የወጪና ገቢ ንግድን ለማሳለጥና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ተናግረዋል::
