
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
183 subscribers
About Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Standard Gauge Railway Share Company (Ethio-Djibouti Railway /EDR) was established in April 2017, based on the Bilateral Agreement signed between the two states, the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the Republic of Djibouti with an initial capital investment $500 Million USD. The company has started its work by providing passenger and freight transport services since January 1, 2018. For more information please visit our website: www.edr.gov.et
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

ዛሬ ከሜዲትራኒያን የባህር ማጓጓዣ ኩባንያ (ኤም.ኤስ.ሲ) ጋር በመተባበር 104 ባዶ 20 ጫማ ኮንቴይነሮችን በተሳካ ሁኔታ ከጅቡቲ ወደ እንዶዴ የጭነት ማዕከል በማስገባት የኢትዮጵያን የወጪ ኢኮኖሚ ለማሳለጥ ተዘጋጅተናል! እነዚህ ኮንቴነሮች በቅርቡ ለፕሪሚየም ደንበኞች ያመቻቸነውን የክሬዲት አገልግሎት በመደገፍ እንደ ቡና፣ የቅባት እህሎች እና ሌሎች የወጪ ንግድ ምርቶችን ለማጓጓዝ በእጅጉ ያገለግላሉ። ይህም የሀገር ውስጥ ላኪዎች ምርቶቻቸውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲያደርሱ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋለ። ይሄ ገና ጅምር ነው—የወጪ ንግዳችንን በተቃና ሁኔታ ለማላቅ የምናደርገውን ብርቱ ጥረት በመቀጠል ተጨማሪ ተግባራትን አጠንክረን እንቀጥላለን። ይህንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የሎጂስቲክስ ስራ እንከን የለሽ እና ቀልጣፋ ያደረጋችሁ ቁርጠኛ ሠራተኞቻችን፣ ለኤምኤስሲ አጋሮቻችን እና ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን እናመሰግናለን።


https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Mg3yLFS35VD6BcXuef99sZmH4AS3bHpYFPPCFKGcbBvMzVGXiTKiJUJ22MrUEaFkl&id=100001846000839&mibextid=wwXIfr

"ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ሁለት ፉርጎ ይዞ በሠዓት 20 ኪሎ ሜትር ያደርግ የነበረው ጉዞ 'ነበረ' ሆኗል ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር ከለውጡ በፊት ሳይሆን ከለውጡ በኋላ እስከዛሬ አራት ዓመት ድረስ ሁለት ፉርጎ ይዞ በሠዓት 20 ኪሎ ሜትር ይጓዝ እንደነበረና ይህ ታሪክ ተለውጦ 'ነበር' ሆኗል ሲሉ ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለፁ። አሁን ላይ ባቡሩን በመሠረታዊ ደረጃ ለመቀየር በተሰሩ ስራዎች በሠዓት 60 ኪሎ ሜትር እንዲጓዝ ማድረግ መቻሉን አክለዋለ። ፍጥነት ከመጨመር ባሻገር በርካታ ፉርጎዎችን የማመላለስ አቅም ላይ ደርሷል። ይህ አቅም መፈጠሩ ጅምር መሆኑን በማስታወስ ከዚህ በላይ ማደግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት - ከመደበኛ እስከ ቻርተርድ !! ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ከመደበኛ የባቡር ጉዞዎች በተጨማሪ ከደንበኞች በትዕዛዝ የሚቀርቡ ልዩ ጉዞዎችን ማቅረብ መጀመሩን ይፋ አድርጓል። በኦንላይን የጉዞ ትኬት በመቁረጥ ከሚደረገው መደበኛ የባቡር ጉዞ በተጨማሪ በምቾት፣ ፈጣን እና አስደሳች የቻርተርድ ባቡር ጉዞ መጀመሩን ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልፀዋል። የቻርተርድ አገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ ሰብሰብ ብለው አስደሳች ጉዞ ለማድረግ፣ የተለያዩ ሁነቶችን አስመልክቶ ለሚደረግ ጉዞ ወይም ድርጅቶች በተለየ መልኩ ለሚያደርጓቸው ዝግጅት በልዩ መልኩ የሚደረግ አስደሳች ጉዞ መሆኑን ጠቁመዋል። ከለቡ እስከ ድሬዳዋ የሀገርዎን መልክአ ምድርና ተፈጥሮን እያደነቁ እንዲጓዙ፤ ጉዞዎን እስከ ጅቡቲ ለማድረግ ካቀዱም በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎቱ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የሚያደርጉት ጉዞ አስተማማኝ እና ምቹ ፤ ተወዳዳሪ እና ተመጣጣኝ ዋጋ የሚጠየቅበት ልዩ የባቡር ውስጥ መስተንግዶን ያካተተ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ገልፀዋል።
