Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 15, 2025 at 04:17 PM
በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የባቡር ደህንነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ውይይት አካሂደናል፤ ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት እየሰጠ የሚገኘው አገልግሎትን በሚገጥሙት የባቡር ደህንነት ስጋቶች ምክንያት እንዳይስተጓጎል ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር አካሂደናል፡፡ ቢሾፍቱ ከተማን የሚያቋርጠው የባቡር መስመር ከk 58 እስከ k 71 ( ከኪሎ ሜትር 58 እስከ ኪሎ ሜትር 71) ባለው የአስራ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚያጋጥሙ የደህንነት ስጋቶችን ለይተናል፡፡ ከተማዋ የምታከናውናቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የባቡር ሀዲዱን እንዳይጎዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ መከናወን እንዳለባቸው ከመግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ የግንባታ ዕቃዎችና የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን ጭነው የባቡር ሀዲዱን የሚያቋርጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች የተለየ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ በውይይታችን አንስተናል፡፡ ተማሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተፈቀደላቸው ማቋረጫ ውጪ በሀዲዱ ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ በጋራ ግንዛቤ በመፍጠር መከላከል እንደሚገባ አንስተናል፡፡ የባቡር ሀዲዱ ባለበት አቅራቢያ እየተስፋፋ የሚገኘው ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ባስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባና የባቡር እንቅስቃሴውን እንዳይገድብ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተግባብተናል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የፀጥታ አካላት፣ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ የከተማ አስተዳደር ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩን አጠናቀናል፡፡
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የባቡር ደህንነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ውይይት አካሂደናል፤  ኢትዮ ...
👍 1

Comments