Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 23, 2025 at 02:36 PM
ደዋንሌ ባቡር ጣቢያ ለባቡር ጭነት አገልግሎት ያለውን አዋጭነት ተመልክተናል፤ በዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የተመራ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን ከድሬዳዋ እስከ ደዋንሌ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ ደዋንሌ ባቡር ጣቢያ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት ለምናጓጉዛቸው በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ኮንቴነሮች ማከማቻነት የሚያገለግል ምቹ ሁኔታ እንዳለው ተመልክተናል፡፡ ከድሬዳዋ፣ሞጆ፣እንዶዴና አዳማ የባቡር ጭነት ጣቢያዎች በተጨማሪ አዳዲስ የጭነት ጣቢያዎችን ለመክፈት የያዝነውን ዕቅድ ከማሳካት አንፃር ደዋንሌ ባቡር ጣቢያ ያለው አቅም ተለይቷል፡፡ በጅቡቲ ወደብ ለአጭርና ለረጅም ጊዜ የሚከማቹ ኮንቴነሮችን በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባትና በደዋንሌ ጣቢያ እንዲከማቹ በማድረግ የጊዜ፣ ወጪና ጉልበት ብክነትን ማስቀረት እንደሚቻል ገምግመናል፡፡ ባቡር ጣቢያው አሁን ያለውን ይዞታ ይበልጥ በማስፋፋትና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚሆኑ አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላት ወደ ስራ የሚገባበትን ሁኔታ ለይተናል፡፡
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): ደዋንሌ ባቡር ጣቢያ ለባቡር ጭነት አገልግሎት ያለውን አዋጭነት ተመልክተናል፤  በዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታከለ...
👍 1

Comments