Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 28, 2025 at 12:25 PM
የባቡር ትራንስፖርት ደህንነትን ለማረጋገጥ በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት፣ ምክክርና ግንዛቤ የማሳደግ ስራን አጠንክረን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ይህን ተግባር ከአርብቶ አደር ዜጎቻችን ጋር በተከታታይ እያከናወንን ነው፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን በባለቤትነት መንፈስ በመጠበቅ ራሳቸውን ብሎም ንብረቶቻቸውን ከባቡር አደጋ እንዲጠብቁ ሰፊ ግንዛቤ እየተሰጠ ነው፡፡ የማህበረሰብ አቀፍ ግንዛቤ ማስጨበጫ የስራ ክፍል (Community Engagement Department) በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ በሶማሌና በአፋር ቋንቋዎች ትምህርትና ግንዛቤ በመፍጠር ትስስራችንን እያጠነከረ ይገኛል፡፡
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): የባቡር ትራንስፖርት ደህንነትን ለማረጋገጥ በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይ...

Comments