Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 29, 2025 at 06:47 PM
ዛሬ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመጡት መንገደኞች ባቡርን ምርጫቸው አድርገው ወደ ድሬዳዋ አብረውን ተጉዘዋል፡፡ በህብረት የተጓዙት ከሰባ በላይ መንገደኞች በባቡር መሠረተ ልማቱ መደመማቸውን፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳፋሪ መመልከታቸውን፣የተቋሙ ሠራተኞች ለደንበኞች ያደረጉት አቀባበል፣ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገር ጋር ያስተሳሰረ ዘመናዊ ባቡር መሆኑን፣ አፍሪካ በ2063 የእርስ በርስ ትስስርን ለማሳካት ለያዘችው ዕቅድ እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ የሚችል መሆኑን መስክረውልናል፡፡ እንደ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ እያወጉ፤ የምስራቁን የሀገራችንን መልክአ ምድር ግራና ቀኝ እየተመለከቱ መጓዝ የሚፈጥረው ስሜት ልዩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እንደ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሁሉ ሌሎች ተቋማትም ሰራተኞቻቸውን ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል በባቡር ቢያጓጉዙ፣ የኮንፈረንስ ከተማ ወደሆነችው አዳማ ቢሄዱ፣ ቢሾፍቱና ሌሎች መዳረሻዎችን ቢመለከቱ የሀገርን አንድ ገፅታ ከመመልከት ባሻገር በአፍሪካ ቀዳሚ የሆንበትን የባቡር ታሪክ ሊረዱበት ይችላሉ ። እኛም እንላለን መርጣችሁ በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ስለተገለገላችሁ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): ዛሬ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመጡት መንገደኞች ባቡርን ምርጫቸው አ...

Comments