Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
May 31, 2025 at 07:51 PM
የልምድ ልውውጥ ተደረገ በቅርቡ የኬንያ ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይና ካምፓኒ ጋር የነበራቸውን የ5ዓመታት የስራ ስምምነት ጨርሰው ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ኋይል ለመስራት የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም አስመልክቷ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በኬንያ ባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ አብዲ ድዋል የተመራው ልዑክ ተሞክሮ ለመቅሰም እንዶዴ ባቡር ጣብያን ጓብኝተዋል፡፡ በእንዶዴ ባቡር ጣብያ ተገኝተው የኦፕሬሽ፤ የጥገና እና የመልቲሞዳል አሰጣጥ ሂደቱን ተዘዋዉረው ተመልክተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ወቅት ከዘርፉ ኃላፊዎች በቀጣይ ላቀዱት ጉዞ የሚረዱ ነጥቦችን አንስተው ተሞክሮዋቸውን አጋርተዋል ፡፡ በመጨረሻም በነበራቸው የሁለት ቀናን ቋይታ በርካታ ተሞክሮዎችን የቀሰሙ መሆኑን ገልፀው፡፡ በቀጣይ ኬንያ ባቡር ኮርፖሬሽን ልክ እንደ ኢትዩ -ጅቡቲ ባቡር ሙሉ በሙሉ በራስ ሀይል ለመስራት ያቀደቸውን ውጥን እውን ለማድረግ የልምድ ልውውጡ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ::
Image from Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR): የልምድ ልውውጥ ተደረገ  በቅርቡ የኬንያ ባቡር ኮርፖሬሽን  ከቻይና  ካምፓኒ  ጋር  የነበራቸውን የ5ዓመታት የ...

Comments