Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 7, 2025 at 06:07 AM
"ከባድ የሆኑ የሎጂስቲክስ ተግዳሮቶችን አልፈናቸዋል"- ታከለ ኡማ
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከባድ የሆኑ የሎጂስቲክሰ ተግዳሮቶችን አልፈናቸዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በዘርፉ ካሉን እድሎች አንፃር በጣም ከባድ የሆኑትን የሎጂስቲክስ ተግዳሮቶች አልፈን ሰፊ የገበያ ዕድሎችን መጠቀም እየጀመርን ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ያላትን እምቅ አቅም ወደ ዓለም ገበያ በማቅረብ ረገድ ሰፊ አቅማችንን እየተጠቀምን እንገኛለን በዚህም ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና የተቀረው ዓለም በኢትዮጵያን ምርት ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ዕድሎችን ፈጥረናል፡፡
በዚህ ረገድ የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን በብልሃት እየጣስን ወደፊት እንገሰግሳለን ብለዋል፡፡
በሎጂስቲክስ ዘርፉ ከዚህ ቀደም ካጋጠሙንና ካለፍናቸው መሰናክሎች አንፃር የመጪው ተግዳሮት በጣም ትልቅ አይሆንም ብለዋል::