
Ethio-Djibouti Railway Share Company (EDR)
June 7, 2025 at 01:12 PM
የአብሮነት መድረክ- በሮሊንግ ስቶክ
ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ካሉት በርካታ የሥራ ክፍሎች መካከል አንዱ በሆነው የሮሊንግ ስቶክና ሜንቴናንስ የሥራ ክፍል ( የባቡር ጥገናና ስምሪት የስራ ክፍል) የሰራተኞች አብሮነት መድረክ ተካሂዷል::
በመድረኩ የሮሊንግ ስቶክ ባለፉት አምስት ወራት ያስመዘገባቸው ስኬቶችን ይበልጥ ማሳደግ የሚቻልባቸው ሃሳቦች ተነስትዋል::
የስራ ክፍሉ ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ በመውጣት አስተማማኝ የከፍታ ጉዞ እያደረገ እንደሚገኝ የስራ ክፍሉ ሠራተኞች ተናግረዋል::
በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የኦፕሬሽን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ የባቡር ሞተርን እና ፉርጎዎችን በተሳካ ሁኔታ ጠግነው ለአገልግሎት ብቁ ከማድርግ ጀምሮ በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ለሎጂስቲክስ ዘርፉ መሳለጥ አይነተኛ ሚና መጫወታቸ ተብራርቷል::
ለተመዘገበው ስኬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለሰጡት በሳል የስራ መምሪያና ላደረጉት የቅርብ ድጋፍና ክትትል ሠራተኞቹ ምስጋና አቅርበዋል::
በዕለቱ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችና የዕውቅና መርሀግብር ተካሂዷል::
