
EthioTube
May 22, 2025 at 06:47 AM
መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ
የጤና ሚኒስቴር ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ ነው ብሏል
‹‹የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት በቅርበት እየተከታተልኩ ነው›› የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የመላው አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ እናት ፓርቲና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ አሳሰቡ፡፡
አራቱ ፓርቲዎች ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የጤና ባለሙያዎች የሚያገኙት ገቢ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማኖር እንዳልቻለ ገልጸው ለአንድ ወር ያህል ሲያቀርቡት ለነበረው ጥያቄ መንግሥት ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ ተስፋ በማድረግ፣ እንዲሁም የባለሙያዎቹን ማሳሰቢያ ተከትለው በጉዳዩ ላይ ሐሳብ ከመስጠት በመቆጠብ በጥንቃቄ ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/141540/
#ethiopia #ethiopiandoctors
