EthioTube
EthioTube
June 9, 2025 at 04:31 AM
"ባለቤቴ ዘረፈኝ! ጎዳና ልወጣ ነው ድረሱልኝ" አትሌት ገለቴ ቡርቃ አትሌቷ በሩጫ ዘመኗ ያገኘችውን ሀብትና ንብረት ባለቤቷ መውሰዱን ገልጻ፣ "ጎዳና ልወጣ ነው መንግስት ይድረስልኝ" ብላለች። መኖሪያ ቤት እና መንግስት በተለያየ ጊዜ የሸለማት 11 መሬቶች ውስጥ አስሩ ባለቤቷ መሸጡን እና አሁን ካለችበት ቤት ለማስወጣት በፍርድ ቤት ጉዳዩን እየጨረሰ ነው ብላለች። ካሏት 5 መኪናዎች 4 መኪኖችን ባለቤቷ መሸጡንም ገልጻለች። በአሁኑ ወቅት ልምምድ አቁማ በፍርሃት ለአንድ አመት ከቤት ሳትወጣ መቀመጧን ተናግራለች። "ፍርድ ቤት ሁሉንም ነገር እኔ ላይ እየፈረደ ነው የእኔን ጉዳይ እየተመለከተ አይደለም" በማለት በገመዳ ሾው ላይ ቀርባ ተናግራለች። መንግስትና ህዝብ ይድረስልኝ ስትልም ጠይቃለች። (Source: Ethiopian Women in Sports)
Image from EthioTube: "ባለቤቴ ዘረፈኝ! ጎዳና ልወጣ ነው ድረሱልኝ" አትሌት ገለቴ ቡርቃ  አትሌቷ በሩጫ ዘመኗ ያገኘችውን ሀብትና ን...

Comments