
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
June 13, 2025 at 01:45 PM
በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ላይ የተካሄደ የባለሙያዎች ውይይት
...
በሀገር አቀፍ ደረጃ የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል የተጀመሩ ጥረቶች ውጤት እንዲያስገኙ ኢሰመኮ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረጉን ይቀጥላል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ረገድ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ የባለሙያዎች ውይይት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።
ኢሰመኮ ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን አስመልክቶ ባካሄደው ብሔራዊ ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ላይ በዘርፉ ከሚሠሩ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት፣ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤቶች፣ የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማእከል እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተውጣጥቶ የተቋቋመው የባለሙያዎች ኮሜቴ አባላት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ እና የዴንማርክ ሰብአዊ መብቶች ተቋም ተወካዮች በውይይቱ ላይ በአማካሪነት ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ፍትሕ ሚኒስቴር በተለያዩ የውይይት መድረኮች በተሰጡ አስተያየቶችና ግብአቶች መሠረት ያሻሻላቸው የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ይዘቶች ለኮሚቴው ቀርበው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=33424
#ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
