
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
June 17, 2025 at 09:21 AM
⚠️ለጥንቃቄ ⚠️
✅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለዜጎች ምቹ፣ ዘላቂና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገር እና በርቀት የሥራ ዕድሎች ያሉ አማራጮችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም ተገኝተውበታል፡፡
🚨ከአሳሳች ማስታወቂያዎች ራስዎን ይጠብቁ❗️
✅ህገወጦች 🇨🇦ካናዳና 🇪🇺አውሮፓን ጨምሮ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው ሀገራት እንልካለን የሚሉ አሳሳች ማስታወቂያዎችን እያሰራጩ ይገኛል፡፡ ይህም ዜጎችንን ላልተገባ እንግልትና ወጪ እንዲሁም ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚዳርግና ህይወትዎን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ነው፡፡
✅እርስዎም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎቱ ካልዎት ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዲሁም ለከፋ አደጋ ከሚዳርግዎ ህገ-ወጥ ዝውውር እራስዎን እንዲጠብቁ እየገለጽን የሚከተሉትን መረጃዎች ልብ እንዲሉ እናሳስባለን!
🌍 የሁለትዮሽ ስምምነት የተገባባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ❓
✅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሁን ወቅት ህጋዊ የሥራ ስምሪት እየሰጠባቸው የሚገኙ ሀገራት የሚከተሉት ሀገራት ናቸው፡-
1️⃣ሳዑዲ አረቢያ🇸🇦
2️⃣የተባበሩት አረብ ኤሚሬት🇦🇪
3️⃣ሊባኖስ🇱🇧
4️⃣ኳታር🇶🇦 እና
5️⃣ኩዌት🇰🇼 ናቸው፡፡
📢ልብ ይበሉ❗️
❌ ከላይ ከተጠቀሱት ሀገራት ውጪ ህጋዊ የሥራ ስምሪት የሚሰጥባቸው ሀገራት የሉም፡፡
✍️ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን👇
📚 የውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡
📚ከዚህ ባለፈ ወቅታዊና በቂ መረጃ ይኑርዎ! ለዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊ ድረ-ገጽን፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽን፣ የብሔራዊ መገናኛ ብዙሃንን እና ተዓማኒነት ያላቸው ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን እንደ መረጃ ምንጭነት ይጠቀሙ፡፡ አልያም አቅራቢያዎ በሚገኙ የክልል፣ የከተማ አስተዳደርና በየደረጃው ያሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መዋቅሮች በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ!
🛑 አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የህግ አስከባሪ አካላትና በየደረጃው ለሚገኝ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መዋቅር ያሳውቁ❗️
📢 ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ♻️
✅ ሌሎችም ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይጋለጡ ያድርጉ❗️
ሰኔ 10፤ 2017
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com
