Elias Meseret
June 11, 2025 at 06:55 PM
#መልካምዜና የሁላችሁም ድምፅ የሆነው መሠረት ሚድያ ከእኔ ጫንቃ እና ኪስ ተላቆ ራሱን ችሏል 🎊
ምናልባትም በሀገራችን የሚድያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ሙሉ በሙሉ ከአባልነት (subscription) በሚገኝ መዋጮ ላይ ብቻ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስ እንዲሆን ታስቦ የዛሬው ወር የተጀመረው ስራ ተሳክቷል።
ለዚህ የሚሆን በቂ ሰዎች subscriber ሆነዋል፣ ለሪፖርተሮች ክፍያ እና ሌሎች ወጪዎች ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ሚድያ ሆኗል ማለት ነው። ይህም ሚድያው ከተመሰረተ በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ከህዝብ ላገኘው ተቀባይነት ትልቅ ማሳያ ነው።
ከዚህ በኋላ 'subscribe አርጉ' ከተባለ ለሚድያው ድጋፍ ለማረግ ሳይሆን ልዩ መረጃዎችን እና የምርመራ ዘገባዎችን ከመሠረት ሚድያ እንድታገኙ ለመጠቆም ብቻ ይሆናል። ሊንክ: https://substack.com/@meseretmedia
ሁላችሁንም በሚድያው ስም አመሰግናለሁ 🙏🏽
❤️
👍
🙏
18