
Elias Meseret
41.1K subscribers
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

ቅጣት እንደ ቋሚ ገቢ ምንጭ? ለምን በሌላው ሀገር እንደሚደረገው በመጀመርያ ለህዝብ በስፋት ግንዛቤ መፍጠር፣ ከዛ ፕላስቲኮችን ሰብስቦ ለ recycling እንዲውሉ ከሳንቲም ጀምሮ ክፍያ እንዲኖረው ማትጊያ/ማበረታቻ ማዘጋጀት፣ ምናልባት ይህ ካልተሳካ በመጨረሻ ወደ ቅጣት አይኬድም (ቅጣት የሚባል ነገር ብዙ ሀገራት ከነጭራሹ ባይኖርም? ነው ወይስ ቅጣት በይፋ የመንግስት የገቢ ምንጭ እንዲሆን ታስቧል?


መሬት ላይ እየሆነ ካለው ነገር ባልተናነሰ እውነታውን ለመሸሸግ የሚደረገው ሙከራ ያሳስባል!


እንደዛማ ከሆነ እኔም የደሞዝ ጥያቄ አለኝ! እስካሁን ከኪሴ ገንዘብ እያወጣሁ እና በነፃ እያገለገልኩ ያቋቋምኩት መሠረት ሚድያ ከዚህ በኋላ ደሞዝ ሊከፍለኝ ስለሚገባ Subscribe አርጉ፣ እድሜ ልክ በነፃ ማገልገል የለም 🙃 ⤵️ https://substack.com/@meseretmedia


ከመንግስት እና ከግል ሰራተኞች ደመወዝ ላይ 'ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ' ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረው ሀሳብ መቅረቱ ተሰምቷል! በዚህ የኑሮ ውድነት ይህን የሌለ ሀሳብ ያመጣውን ግለሰብ ነበር ህገ መንግስታዊ ስርዐቱን በሀይል ለመናድ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑ የውጭ ሀይሎች ጋር በመተባበር እና የከተማ ውስጥ ሁከት ለማነሳሳት በማሴር የሚል ጠብሰቅ ያለ ክስ መክሰስ።

ክፋት በሩ ላይ እንደሚጠብቀው እያወቀ እንኳን ያመነበትን ከመናገር ወደኋላ የማይለው አቶ ታዬ ደንደአ! ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ማህበራዊ ሚድያ ላይ መግለፅ ለእስር ከዳረገ ለሌላው ዜጋ የሚሰጠው መልእክት ምንድን ነው?


እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ!


#ዜናመሠረት የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መታሰሩ ታወቀ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ገልጿል። https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/82f?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g

#አስደሳችዜና መኪና እያሽከረከሩ፣ ስራዎትን እየሰሩ ወይም ዎክ እያረጉ የመሠረት ሚድያ መረጃዎችን ማዳመጥ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ መሠረት ሚድያ ከዛሬ ጀምሮ መረጃዎቹን በፅሁፍ ከማቅረብ በተጨማሪ በድምፅ/ፖድካስት ይዞላችሁ እንደሚቀርብ ሲያበስር በደስታ ነው። ከዚህ በኋላ ከፋይ አባሎቻችን (Paid Subscribers) የትኛውም ቦታ ሆነው በቀጥታ በኢሜይላቸው ወይም በሶሻል ሚድያ ሊንኮች አማካኝነት የሚያገኟቸውን ፖድካስቶች ከፍተው ማዳመጥ (stream ማድረግ) ይችላሉ። ዛሬውኑ ይቀላቀሉን ⤵️ https://substack.com/@meseretmedia


"በቴሌኮም ዘርፍ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ" ውድድሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጋር ከሆነ ታድያ ከማን ጋር ተወዳድሮ ነው? ኧረ ተዉ ግን 🤔


በዚህ ምክንያት ህይወቱን ያጣ፣ ኑሮው የተመሳቀለ እና የማይወጣው ችግር ውስጥ የገባው ብዙ ነው። እነዚህ ዜጎች አሁንም ፍትህ የማያገኙ ከሆነ የምርመራ ዘገባው ከጀርባ ሆነው ይህን ድርጊት ከለላ የሰጡት ላይ ትኩረት በማድረግ ይቀጥላል። https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/33c?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g