
Elias Meseret
June 18, 2025 at 12:46 AM
#ሰላምወዳጆች የህግ ትምህርት ቤት እያለን መምህራችን የነበረው ሀሰን መሀመድ (ሀሰኖ) ከፍ ያለ ህመም አጋጥሞታል። ከዋነኞቹ ኦርጋኖቹ በተለይ ሁለቱ (ኩላሊት እና ጉበት) ንቅለ ተከላን ጨምሮ ሌሎች የውጪ ሀገር ሕክምና ይፈልጋሉ። ለዚህ ሕክምና የሚያስፈልገውን ወጪ ብቻውን እንደማይችለው ታውቋል።
ከወዳጆች ውጪ ሌላ የሚኬድበት ቦታ የለምና በአንድም በሌላ አጋጣሚ ያወቃችሁት፣ ያስተማራችሁ፣ ያማከራችሁ፣ የረዳችሁ፣ ፈገግ ያስባላችሁ፣ ጩኸታችሁን ያሰማላችሁ፣ ሀሳባችሁን የገለፀላችሁ፣ በአጠቃላይ የሀሰኖ አሻራ በአዕምሮ፣ በልብ እና በሕይወታችሁ ያረፈ ሰዎች ሁሉ አሁን የሀሰኖን ሕይወት ለማዳን ትብብራችሁ ይፈለጋል።
በግል 15 ሺህ ብር አስገባለሁ፣ ሁላችን ተረባርበን ሀሰኖን አለህ እንበለው። አስተዋፅኦ ማድረጊያ ቁጥሮቹ (ንግድ ባንክ እና Zelle) በምስሉ ላይ ተቀምጧል።
ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ።

🙏
👍
8