Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
June 9, 2025 at 10:58 AM
ሚሲዮኑ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር ተወያየ፤ (ሰኔ 2/2017 ዓ.ም) ሚሲዮኑ የትራንስፖርት ሚንስቴር ተወካይም እና የማሪታይም ባለስልጣን የጅቡቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ በተገኙበት ከኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር በስራ ቅንጅት፣ በስነ-ምግባር እና በአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት አድርጓል። ሚሲዮኑ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው የሀገራችን ገቢ-ወጪ ምርት የማጓጓዝ ሂደት ላይ ያሉ የአሠራር ክፍተቶችን በመለየት፣ የሎጂስቲክ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እና በውስጣዊ ቅንጅት ላይ በቅርበት ለመስራት እንዲቻል ውይይቱ ተገቢ መሆኑን ገልጿል። የአሽከርካሪዎች ማህበራት ተወካዮች በበኩላቸው በኮሪደሩ መሠረተ-ልማት የሚጋጥሙ እክሎች፣ የስራ መስተጓገል፣ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ እና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቅሰዋል። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይም ከአሸከርካሪዎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች አገልግሎትን ለማሳለጥ አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በተገቢው አሠራር መሠረት በፍጥነት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል። በመጨረሻም ሚሲዮኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ ቴክኒካል ችግሮችን በየጊዜው በመወያየት እና አገልግሎትን በተቀናጀ መልኩ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳውቋል።
Image from Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ: ሚሲዮኑ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር ተወያየ፤  (ሰኔ 2/2017 ዓ.ም) ሚሲዮኑ የትራንስ...

Comments