
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
June 11, 2025 at 07:52 AM
ጣናነሽ 2 ጀልባ አዳማ ከተማ ደርሳለች።
ጣናነሽ 2 ጀልባ አዳማ ስትደርስ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላታል።
መጋቢት 30 ከጂቡቲ ዶላሬ ወደብ ተነስታ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞዋን የጀመረችው ጣናነሽ 2 ጀልባ፤ ባለፉት 2 ወራት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ መልከዓ ምድር እያለፈች ጥንቃቄ የታከለበት ጉዞ እያደረገች ትገኛለች።
ግንቦት 7 ቀን ወደ ኢትዮጵያ ከገባች ጀምሮ ላለፉት አንድ ወር ገደማ በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞችን እያቆራረጠች ነበር ጉዞዋን ስታደርግ የቆየችው።
በዛሬው ዕለት ደግሞ አዳማ ከተማ ገብታለች።
ይህች መርከብ በግዝፈቷም በአይነቷም ለየት ያለች ስትሆን፤ ለኢትዮጵያም ከጀልባነት በላይ ብዙ ተምሳሌታዊ ትርጉም አላት።
150 ሜትሪክ ቶን የምትመዝን ክብደት ሲኖራት ርዝመቷም 38 ሜትር ያህል ነው፤ 188 ሰው የመጫን አቅሟም አላት።
የጀልባዋ ወደ ሀገር መግባት እና ሥራ መጀመር፤ በውሃ ትራንስፖርት፣ አጠቃላይ በውሃ ቱሪዝም እና በማሪታይም አገልግሎት ላይ የራሱን የሆነ ከፍ ያለ ድርሻ እና አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
