
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
June 11, 2025 at 04:58 PM
ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በጅቡቲ ከኦሮሚያ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ፤
(ሰኔ 04/2017 ዓ.ም) ምክትል የሚሲዮኑ መሪ ክቡር ከበደ አበራ በጅቡቲ ከኦሮሚያ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በማህበሩ አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም የልማት ማህበሩ በያዘው ዕቅድ መሠረት ከሌሎች ማህበራት ጋር በመቀናጀት በጅቡቲ የሚገኙ ዜጎቻችን የሀገሪቱን ሕግ አክብረው እንዲሰሩ እና በዚህም ማህበሩ አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርግ አሳስበዋል።
