DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 10, 2025 at 10:52 AM
የጀርመንን ዜግነት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ በአንድ ዓመት ውስጥ 291,955 የውጭ ሀገር ዜጎች የጀርመንን ዜግነት ወሰዱ። የጀርመን ዜና ምንጭ ዲፒኤ ዛሬ እንደዘገበው ባለፈው የጎርጎሮሲያኑ 2024 ዓ.ም..የጀርመን ዜግነትን የወሰዱት የውጭ ሀገር ዜጎች ቁጥር ባለፉት 24 ዓመታት ከተመዘገበው እጅግ ከፍተኛ የሚባል ነው። ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው የዜግነት ሕግን ለማዘመን በሥራ ላይ የዋሉ የሕግ ለውጦች ናቸው። በዚህ ህግ መሠረት፤ የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነትን ቢወስዱም የቀድሞ ዜግነታቸውን አይነጠቁም ወይም ጀርመን አትከለክልም። በተጨማሪም የጀርመን ዜግነትን ለመውሰድ ስምንት ዓመት ሳይሆን አምስት አመት ብቻ ጀርመን ውስጥ መኖር በቂ ነው። በስራም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ከኅብረተሰቡ ጋር ፈጥነው የተዋሀዱ የውጭ ዜጎች እንደውም ሶስት ዓመት ብቻ ጀርመን ከኖሩ ለዜግነት ማመልከት ይችሉ ነበር። አዲሱ የጀርመን ጥምር መንግስት ሲመሰረት ግን ይህን ሽሮ ከዚያ በፊት እንደነበረው ከአምስት ዓመት በኋላ እንዲሆን ተስማምቷል። እንደ የጀርመን ፌደራል ስታቲስቲክስ ቢሮ በ2024 የጀርመንን ዜግነት በብዛት የወሰዱት ሶርያውያን ሲሆኑ እነዚህም 28% ያህሉ ናቸው። 8% የቱርክ ፣ 5% የኢራቅ፤ 4% የሩሲያ እና 3% የአፍጋኒስታን ተወላጆች ናቸው። በአጠቃላይ በአማካይ የውጭ ሀገር ዜጎቹ በጀርመን 12 ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ኖረዋል።
Image from DW Amharic: የጀርመንን ዜግነት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ በአንድ ዓመት ውስጥ 291,955 የውጭ ሀገር ዜጎ...
👍 😮 🥅 9

Comments