DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 11, 2025 at 12:16 PM
· ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው ገቡ ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱ ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው ገቡ። ዛሬ ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ሰያካሄዱት በትግራዩ ጦርነት ከምዕራብ ትግራይ እና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው። ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ መንግስት ወደቀዬአችን እንዲመልስን ብንጠይቅም ምላሽ አጥተናል ሲሉ በምሬት ገልፀዋል። ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት በፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት በራፍ ቆመው ምላሽ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ የቆዩ ተፈናቃዮቹ፥ ረፋዱ ላይ ነበር የክልሉን ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ግቢ ጥሰው የገቡት። ተፈናቃዮቹ "ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፥ ከዚህ አንወጣም" ሲሉም ተደምጠዋል ። ዘገባ፥ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
Image from DW Amharic: ·  ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው ገቡ ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱ ተፈናቃዮች ...
😢 👍 😂 4

Comments