DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 12, 2025 at 12:14 PM
ዤንቭ-ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለዉ ህዝብ ከአምናዉ ትንሽ ቀንሷል፤ርዳታ ግን የለም-ተመድ በያዝነዉ የግሪጎሪያኑ 2025 ዓመት ተገድዶ ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለዉ ሕዝብ ቁጥር ከ122.1 ሚሊዮን እንደሚበልጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) እንዳለዉ ዘንድሮ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ የሶሪያ ተፈናቃይና ስደተኞች ወደየቀያቸዉ ተመልሰዋል።በዚሕም ምክንያት ዘንድሮ ሚዚያ ላይ በተደረገዉ ጥናት ተገድዶ የተፈናቀለዉ ሕዝብ ቁጥር ከአምናዉ (ከ2024) መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።እምና የነበረዉ የተፈናቃይ ቁጥር 123.2 ሚሊዮን ነበር። የተፈናቃዩ ቁጥር በመጠኑ ቢቀንስም ለስደተኞችና ለተፈናቃዮች የሚሰጠዉ ርዳታም በእጅጉ በማነሱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ከአምናዉ ክፉኛ ተቸግረዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ርዳታ መቀነሷ፣ ሌሎች ለጋሽ ሐገራት መሰላቸታቸዉና ቅድሚያ የሚሰጡት ወጪ መበራከቱ ለርዳታዉ መቀነሰ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸዉ።ዓለም አቀፉ ድርጅት እንደሚለዉ ዘንድሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሕዝብ የተሰደደ ወይም የተፈናቀለባት ሐገር ሱዳን ናት፤ 14.3 ሚሊዮን።የሱዳን፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክና የጋዛ ጦርነቶች አሁን ባሉበት ከቀጠሉ እስከ 2025 ማብቂያ ድረስ የተፈናቃዩ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ኮሚሽንሩ አስታዉቋል።
Image from DW Amharic: ዤንቭ-ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለዉ ህዝብ ከአምናዉ ትንሽ ቀንሷል፤ርዳታ ግን የለም-ተመድ በያዝነዉ የግሪጎሪያኑ  ...

Comments