DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 15, 2025 at 03:36 PM
በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ ዕቀባ ከጣለባቸው ጎራ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለ። የአሜሪካው ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው በዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የውስጥ ማስታወሻ የጉዞ ዕቀባ ይጣልባቸዋል ተብለው ከሰፈሩ መካከል 25 የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ጅቡቲ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ ሱዳን በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱ መካከል ናቸው። ውሳኔው ተግባራዊ ከሆነ ዜጎቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዕቀባ የተጣለባቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 48 ያደርሰዋል። ባለፈው ሰኞ ገቢራዊ በሆነው የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ ኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክል ገደብ ተጥሎባቸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የተፈረመው እና ዋሽንግተን ፖስት ተመለከትኩት ያለው የውስጥ ማስታወሻ የጉዞ ዕቀባ ሊደረግባቸው ይችላል በተባሉት 36 ሀገራት ለሚሰሩ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች የተሠራጨ ነው። በማስታወሻው ኢትዮጵያን ጨምሮ 36ቱ ሀገራት የቪዛ ዕቀባ እንዳይጣልባቸው በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን በ60 ቀናት ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው መገለጹን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ሀገራቱ ቅድመ ሁኔታዎቹን ካላሟሉ ሙሉ ወይም ከፊል የቪዛ ዕቀባ ይጠብቃቸዋል። https://shorturl.at/GPlab
❤️ 👍 2

Comments