DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 15, 2025 at 04:39 PM
የሰኔ 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና • በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ ዕቀባ ከጣለባቸው ጎራ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለ። የአሜሪካው ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው በዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የውስጥ ማስታወሻ የጉዞ ዕቀባ ይጣልባቸዋል ተብለው ከሰፈሩ መካከል 25 የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ጅቡቲ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ ሱዳን በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱ መካከል ናቸው። • በጋዛ ሠርጥ በእስራኤል እና በአሜሪካ ድጋፍ ምግብ በሚታደልበት ቦታ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። • እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረ። የእስራኤል ጦር የሀገሪቱ ዜጎች ከሕዝባዊ አደባባዮች በመራቅ ጥበቃ በሚደረግላቸው አካባቢዎች እንዲቆዩ አሳስቧል። ኢራን በበኩሏ መስጂዶች፣ የባቡር ጣቢያዎች እና ትምህርት ቤቶች ከዛሬ እሁድ ጀምሮ ከእስራኤል ጥቃት የሀገሬው ሕዝብ መሸሸጊያ እንደሚሆኑ አስታውቃለች። በሚሳይሎች እና ድሮኖች ጭምር የሚደረገው የእስራኤል እና የኢራን ውጊያ ሦስተኛ ቀኑን ሲይዝ አንዳቸው በሌላቸው ላይ ብርቱ ጥቃት ለመፈጸም እየዛቱ ናቸው። • የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ ላይ የእስራኤል እና የኢራንን ግጭት ለማቆም በአራት ጉዳዮች ላይ ከሥምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ። የሁለቱ ሀገሮች ውጊያ በካናዳ በሚካሔደው የቡድን ሰባት ሀገራት ጉባኤ ዋንኛ መነጋገሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። • በሰሜናዊ ሕንድ ኡታራክሐንድ የተባለ ግዛት ሔሊኮፕተር ተከስክሶ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ። በሒማሊያ ግዛት የተከሰከሰው ሔሊኮፕተር በሒማሊያ ተራሮች ላይ በሚገኝ ታዋቂ የሒንዱ መንፈሳዊ ጉዞ መስመር እየበረረ እንደነበር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በአደጋው አምስት መንገደኞች አንድ ሕጻን እና የሔሊኮፕተሩ አብራሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦ https://shorturl.at/U2lWV
👍 ❤️ 7

Comments