
DW Amharic
June 16, 2025 at 01:00 PM
የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ በምን ሁኔታ ላይ ነው?
ለቀጣዩ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ለመዘጋጀት ከዛሬ ሰኞ አንስቶ ለ10 ቀናት የሚዘልቅ ውይይት በጀርመን ቦን ከተማ መካሄድ ጀመረ። የዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከፓሪሱ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት የመውጣት ውሳኔ የስብሰባው ዋና መነጋገሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ዋናው የዓለም የዓየር ንብረት ጉባኤ መጭው ዓመት ህዳር ወር ብራዚል ውስጥ ይካሔዳል። ለዚህ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ነው በተባለው በዚው የቦን ጉባኤ ላይ
በርካታ የመንግሥት ተወካዮች እና የአየር ንብረት ባለሙያዎችን ጨምሮ ከ5,000 በላይ ተሳታፊዎች ከሞላ ጎደል ከሁሉም የዓለም ሃገራት ተሳታፊ ይሆናሉ።
በቦኑ አጀንዳ ላይ ከተቀመጡት አንገብጋቢ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ለድሃ ሀገራት እንዴት በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ዕርዳታ እውን ሊሆን ይችላል የሚለው ነው።
በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ውስጥ በተካሄደው በባለፈው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአየር ንብረትን ተከትሎ ለደሃ ሃገራት የሚደረገውን ዕርዳታ በከፍተኛ መጠን ለማሳደግ ተሳታፊ ሃገራቱ ቢስማሙም ገንዘቡ በትክክል እንዴት መከፋፈል አለበት በሚለው ላይ ወጥ አቋም የለም።
ከዚህም በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት መውጣቷን ተከትሎ ስብሰባው ፈተና የበዛበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ዩናይትድ ስቴትስ ገና በመጀመርያው የዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን ነው ከስምምነቱ አፈንግጣ የወጣችው።

👍
❤
❤️
👮♂
8