DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
June 17, 2025 at 05:47 PM
የሰኔ 10 ቀን 2017 አርእስተ ዜና -ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ዘገባ አጋለጠ። --በእስራኤል የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሙሉ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ወይም በተቻለ ፍጥነት እስራኤልን በድንበር በኩል አቋርጠው እንዲወጡ አሳሰበ። በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደዉ ጥቃት በመቀጠሉ ጋና ዜጎቿን ከኢራን ማስወጣት ጀመረች። --ቡድን ሰባት በመባል የሚታወቁት ሰባቱ የበለፀጉት ሀገራት መሪዎች ትናንት ካናዳ ላይ የጀመሩትን ጉባኤ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠሉ ነዉ። -- የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸዉ በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚካሂደዉ ግጭት ተከትሎ ለአስቸኳይ ጉዳይ ጉባኤዉን አቋርጠዉ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል። ሙሉዉን ዜና የድምጽ ማድመቻ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! https://shorturl.at/K62ON
❤️ 🇮🇷 😉 9

Comments