
DW Amharic
June 18, 2025 at 08:58 AM
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት« የመርማሪዎችን የወንጀል ተጠያቂነት ያጠበበ» የሚል ጥያቄ የተነሳበት ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በ3 ተቃውሞና በ1 ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድንፅ አፅድቆታል። በዚህ ዐዋጅ መሠረት መሰል ወንጀሎችን ለመመርመር የተመደበ ሰው በሥራ ላይ እያለ "ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም" በሚል መደንገጉ ጥያቄ አስነስቷል። ይህ ድንጋጌ በምርመራ ሽፋን የመንግሥት ተቃዋሚዎችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን እና ነጋዴዎችን ለማጥቃት የተረቀቀ እና የዜጎችን መብት የሚጎዳ ነው የሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።
አዋጁን ያዘጋጁት አካላት ግን የሕጉ መንፈስ ይህ አለመሆኑን ጠቅሰው አላማው ሽብርተኝነትን መከላከል ነው ብለዋል። እናንተስ ምን ትላላችሁ? ተወያዩበት።

👍
1