
DW Amharic
June 18, 2025 at 10:47 AM
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ሐገራቸው በኢራን ላይ የምትፈፅመው ጥቃት የኒኩለር መርሃ ግብሯን ለማስቆም ብቻ ሳይሆን የመንግስት አመራሩንም ለማፈራረስም ያለመ ነው አሉ።
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር በኤክስ ገጻቸውን የጻፉትን ጠቅሶ የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው «አምባገነን መንግስታት የሚወድቁት በዚሁ መንገድ ነው» ብለዋል።
እስራኤል በአለፈው ሰኞ በቀጥታ ሥርጭት ላይ የነበረን አንድ መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣብያን በቦምብ አጥቅታለች። በጥቃቱ በቁጥር ያልተገለጹ በርካታ ሰዎች መሞት መቁሰላቸውን ዜናው አክሏል።
እስራኤል በቴህራን ወታደራዊ ተቋማት አካባቢ የሚኖሩ ኢራናውያን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በሰቸችው ማሳሰቢያ መሰረት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካመኒ ከተወሰኑ ሰዓታታት በኋላ በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
