
DW Amharic
June 18, 2025 at 11:39 AM
የተፈናቃዮች ስሞታ
ባለፉት አምስት ዓመታት ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን እና ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ 15 የመጠለያ ጣቢያዎች እና ማህበረሰቡ ጋር በመንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚደረግላቸው ድጋፍ ኑሯቸውን የሚመሩ ከ65000 (ስልሳ አምስት ሺ) በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡
በተለይም በባለፉት 2 አመታት የድጋፍ ሁኔታው መቃዘቀዝ የታየበት በመሆኑ እና በመንግስት የሚሰጠን ትኩረት አናሳ መሆን ኑሯችንን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለመምራት ስላላስቻለን ቀድመን በተወለድንበት ሀብት ንብረት ባፈራንበት አካባቢ ተመልሰን እንድንሰራ መንግስት ሊያመቻችልን ይገባል ሲሉ በተሁለደሬ ወረዳ ጃሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ያሉ ተፈናቃዮች ለዶይቼቨለ ተናግረዋል፡፡
በ11መጠለያ ጣቢያዎች እና ከማህበረሰቡ ጋር የሚኖሩ ከ34,000 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የያዘው የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊ ሰይድ ከዚህ ቀደም ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስ ሙከራ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም ማለታቸውን ወኪላችን ኢሳያስ ገላው ከደሴ ዘግቧል፡፡

👍
😢
3