
DW Amharic
June 18, 2025 at 12:10 PM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተወያዩ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
ፓርቲዎቹ እያንዳንዳቸው አራት ተወካዮችን በውይይቱ እንዲያሳትፉ ዕድል ተሰጥቷቸዋል። በሌላ በኩል ግብዣውን ያልተቀበሉ፣ በውይይቱም ያልተሳተፉ ፓርቲዎች መኖራቸው ታውቃል።
በውይይቱ ከተሳተፉ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ኢሕአፓ "ጥያቄ የመጠየቅ ዕድል አላገኘሁም፣ በሌሎች ፓርቲዎች የቀረቡ ጥያቄዎችም መሠረታዊ አይደሉም" በሚል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከመስጠታቸው በፊት ተወካዮቹ መድረክ ረግጠው መውጣታቸውን አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ "ከየመጡበት አካባቢ የሚነሱ የተለያዩ ሀሳቦችን በማዳመጥ ግብዓት ለመውሰድ የታለመ" ያሉትን ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል ሲል ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

😂
1