
DW Amharic
June 18, 2025 at 01:40 PM
ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ
መንግስት ድህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ወደቀዬአቸው የማይመልሳቸው ከሆነ የራሳቸው እርምጃ እንደሚወስዱ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ገለፁ። በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በመንግስት ላይ ተቃውሟቸው የሚገልፁበት ትእይንት ዛሬ በመቐለ ማድረግ የጀመሩ ሲሆን በመጪው ዓርብ የዚሁ አካል የተባለ ሰልፍ በጄኔቫ እንደሚደረግ አስተባባሪዎች አስታውቋል። ተፈናቀዮቹ
ዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀንና ለሊት የሚቆይ ተቃውሞ በመቐለ ሮማናት አደባባይ ማድረግ የጀመሩት እነዚህ የጦርነቱ ተፈናቃዮች፥ ለአምስተኛ ክረምት በመጠለያ መቆየት እንደማይሹ፥ የኢትዮጵያ መንግስት እና የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ለጉዳያቸው የመጨረሻ ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ የራሳቸው እርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል ሲል ሚልዮን ሃይለስላሴ ከመቐለ ዘግቧል።

👍
3