
DW Amharic
June 18, 2025 at 01:55 PM
እስራኤል በቴህራን የሚገኘውን የሐገር ውስጥ ደህንነት መስሪያቤት ማውደሟን አስታወቀች። የእስራኤል ሰራዊት ዛሬ ባሰራጨው መረጃ «የሐገር ውስጥ የደህንነት መስሪያቤቱን ያወደምኩት በጦር አውሮፕላኖች ድብደባ ነው» ብሏል።
ሰራዊቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ በኢራን ላይ የሚካሄዱ ጥቃቶች አላማ የኒኩለር ማብለያ ተቋማትን ማውደም ብቻ ሳይሆን «አምባገነን» ያለውን የኢራንን መንግስታዊ መዋቅሮችንም እንደሚያካትት ገልጾ ነበር ሲል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

👍
🇮🇷
❤
❤️
7